ማን ነው የሚደውልልኝ? አንዳንዶቻችን ድንገተኛ ነገር እንወዳለን፤ አንዳንዶቻችን ደግሞ አንወድም። ማንም የማይወደው አንድ ነገር ግን አለ፤ ልንሸሸው ከምንሞክረው ሰው የመጣን ጥሪ ማንሳት።
ድሮ ሁላችንም ጓደኛ ብቻ ይሆናል ብለን ተስፋ እያደረግን ገቢ ጥሪዎችን በጭፍን ለማንሳት እንገደድ ነበር፤ ዛሬ ግን «ማን ነው የሚደውልልኝ?» ብለን ራሳችንን መጠየቅ፣ የማይታወቅ ቁጥር ስናይም መጨነቅ አያስፈልገንም።
Me በሌላው ጫፍ ስላለው ደዋይ የተቻለውን ያህል ብዙ መረጃ ለመስጠት ይሠራል።
ብልሁ የደዋይ መለያችን ጥሪውን እና ደዋዩን ይለያል፤ እርስዎን ለማገዝም የጥሪውን ዓይነት መድቦ ምልክት ያደርጋል።
ቀላል እና ፈጠራ የተሞላበት፣ የስልክዎን ማያ ገጽ የማያውክ የደዋይ መለያ ሠርተናል፤
Me እስካሁን የለዎትም? አሁኑኑ ያውርዱ


በጥሪ ላይ እያሉም የተለያዩ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ያስችልዎታል።
ስለዚህ «ማን ነው የሚደውልልኝ?» ብለው ከመገረም ይልቅ ስለ ደዋዩ ማንነት እና ስለ ጥሪው አስተማማኝነት በራስ-ሰር ማሳወቂያ ያገኛሉ።
በተጨማሪም Me ከደዋዩ ጋር የሚጋሯቸውን እውቂያዎች (የጋራ እውቂያዎች) እንዲያዩ የሚያስችል በዓለም ላይ ብቸኛው የደዋይ መለያ መተግበሪያ ነው፤ የደዋዩን የማኅበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች እና ሌሎችንም ያቀርብልዎታል።
የደዋይ መለያ የማወቅ ጉጉትን ማርኪያ ብቻ ሳይሆን የደኅንነትዎም ጉዳይ ነው።
የምንኖረው በቴክኖሎጂ በተራቀቀ ዓለም ውስጥ ነው።
እንደ አለመታደል ሆኖ ሁሉም ሰው መልካም ዓላማ የለውም።
አንዳንዶች ዛሬ ያሉንን መሣሪያዎች ለክፉ ዓላማ እና ለማጭበርበር ይጠቀሙባቸዋል።
Me አስቀድሞ ያስጠነቅቅዎታል፤ አጭበርባሪዎች እንዳያታልሉዎት የሚያከብድባቸውን መረጃ ይሰጥዎታል፤ ካስፈለገም አጠራጣሪ ጥሪዎችን በፍጥነት ሪፖርት እንዲያደርጉልን ያስችልዎታል።
Me ለእርስዎ አገልግሎት የሚውል ግዙፍ የመረጃ ቋት አለው።
ቁጥሮችን ለመፈለግ የMe የመደወያ ሰሌዳን ይጠቀሙ፤ ተጨማሪ ዝርዝሮችን
እና መገለጫዎችን ያግኙ።
የደዋይ መለያ መተግበሪያችንን በiPhone፣ በAndroid መሣሪያዎች እና በMe Web መድረክ ላይ እናቀርባለን
ከላይ የተጠቀሱት ባህሪያት በሙሉ በማንኛውም ጊዜ ሊበሩ እና ሊጠፉ ይችላሉ።
Me ሕይወትዎን ለማቅለል እና ከመረጧቸው ሰዎች ጋር ያለ ምንም ውጣ ውረድ በፍጥነት እና በብቃት እንዲገናኙ የተሠሩ ብዙ የተለያዩ ባህሪያትን ይዟል።
የደዋይ መለያ መተግበሪያ አገልግሎታችን ለiPhone እና ለAndroid በነፃ ነው
እኛ በMe ለተጠቃሚዎቻችን ምርጡን አገልግሎት የሚሰጡ እና የደዋይ መለያን ወደ ቀጣዩ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ተጨማሪ ባህሪያትን ለማሻሻል እና ለማዳበር ዘወትር እንሠራለን።
