የጥሪ ማጠቃለያ፦ የምንኖረው በፍጥነት በሚጓዝ ዓለም ውስጥ ነው።
ሁሉም ሰው ሥራ በዝቶበታል፣ ይቸኩላል፣ ጊዜ ያጥረዋል። ዕቅዶች፣ የሚከናወኑ ተግባራት፣ የምንጠብቃቸው ግንኙነቶችና የምንሠራቸው ነገሮች አሉን።
አንዳንድ ተግባራትን በተሳካ ሁኔታና በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቁ የሚያግዝዎ የጥሪ ማጠቃለያ ገጽ።
(ለAndroid ብቻ)
ጥሪው ሲያበቃ አዲሱ «Call Summary» (የጥሪ ማጠቃለያ) ገጻችን በራሱ ብቅ ይላል፤ የሚያስፈልጉዎት አማራጮች በሙሉ ስለሚታዩ ጊዜ ማባከን አያስፈልግዎትም። በአንድ ንክኪ ዝርዝሮችዎን ማጋራትና የWhatsApp መልእክት በሰከንዶች ውስጥ መላክ ይችላሉ።
(WhatsApp ለመላክ ቁጥሩን ሴቭ ማድረግ ፈጽሞ አያስፈልግዎትም)
የጥሪ ማጠቃለያ ገጽ ብዙ ተግባራትን በፍጥነትና በብቃት፣ ሁሉንም በእጅዎ መዳፍ ውስጥ እንዲያከናውኑ ያስችልዎታል። ለምሳሌ፦
ሁሉም በአንድ ንክኪ!
1. የWhatsApp መልእክት መላክ።
2. ቁጥሩን ወደ እውቂያ ዝርዝር ማከል።
3. የጽሑፍ መልእክት መላክ።
4. መልሶ መደወል።
5. የግል ዝርዝሮችን ማጋራት።
6. ቁጥሩን ማገድ።
7. የእውቂያ መረጃን ማጋራት።
8. ለተጠቃሚው ኢሜይል መላክ።
9. ቁጥሩን ወደ ተወዳጆች ማከል።
10. በእርስዎና በእውቂያው መካከል ያለውን የጥሪ ስታቲስቲክስ ማየት
* (ቁጥሩ በእውቂያዎችዎ ውስጥ ከተቀመጠ ብቻ)።
11. የጥሪ ጊዜ።
12. እውቂያውን ማጋራት።
በቀስቶቹ በቅርብ ጊዜ ጥሪዎች መካከል በቀላሉ መንቀሳቀስና ከጥሪ ወደ ጥሪ መዝለል ይችላሉ፤
የደዋዩን ምስል ሲነኩ ደግሞ መተግበሪያው ሙሉ መገለጫውንና ተጨማሪ ዝርዝሮችን ያሳይዎታል።
ከእውቂያው ጋር አካባቢዎን አጋርተው ከሆነ፣ አካባቢውን በገጹ ላይ ማየት ይችላሉ።

ያንኑ ቁጥር እንደገና መደወል ያስፈልግዎታል፤ እንዲያስታውስዎም ይፈልጋሉ?
ችግር የለም! እኛ በMe እናስታውስዎታለን። ምልክቱን ሲነኩ ለአስታዋሽ ጊዜ ሦስት አማራጮች ያሉት ገጽ ይከፈታል፦
- ከአንድ ሰዓት በኋላ።
- ከሁለት ሰዓት በኋላ።
- ነገ በዚሁ ሰዓት።
እንዲሁም የግል ማስታወሻ ማከል ከፈለጉ ይህም ይቻላል። ሥራ እንደሚበዛብዎ እናውቃለን፤ እንዲረሱ አንፈልግም።
ልብ ይበሉ፦
የጥሪ ማጠቃለያ ገጹ ሲከፈት፣ ማያ ገጹን የትም ቦታ መንካት ይዘጋዋል።
ይህ ባህሪ የማይፈልጉት ከሆነ፣ የዚህን ገጽ አጠቃቀም በቀላሉ ማቋረጥ ይችላሉ፦
→ በመተግበሪያው ውስጥ ወደ ቅንብሮች ይግቡ → የጥሪ ማጠቃለያ ገጽን ይምረጡ → ማብሪያ/ማጥፊያውን ይጫኑ!
* አንዴ ካጠፉት በኋላ ገጹ በጥሪ መጨረሻ ብቅ አይልም። *

