ቁጥሮችን ማገድ እጅግ ቀላል ነው። ከማይፈልጓቸው ቁጥሮች የሚመጡ ጥሪዎችን እና የጽሑፍ መልእክቶችን ያስቁሙ!
አዲሱ የMe የማገጃ ሥርዓት
ይህ ባህሪ በነፃ ነው፤ ደግሞም በiOS እና በAndroid መሣሪያዎች ላይ ይሠራል!
ዝምታ ወርቅ ከሆነ፣ ማገድ የወርቅ ቅይጥ ነው
በሕይወትዎ ማንንም አግደው አያውቁም?
እንኳን ደስ አለዎት፤ ወይ በዓለም ላይ ካሉት እጅግ እድለኛው ሰው ነዎት፣ ወይም የድንበርን ትርጉም ያልተረዱ እና ሞባይላቸውን ተጠቅመው ሌሎቻችንን ምስኪኖች ማስቸገር የሚወዱ ሰዎች ገና አላጋጠሙዎትም።
ይህም ካልሆነ ከብረት የተሠሩ ነዎት፤ ማለቂያ የሌለው ትዕግሥትም አለዎት።
እግዜር ይባርክዎ።
ያም ሆነ ይህ አብዛኞቻችን ሰዎችን እንዳያገኙን ማገድ የግድ የሆነብን የሕይወት አጋጣሚዎች ገጥመውናል።
ጉዳዩ የሞባይል ግንኙነት ሲሆን ግን ለማንኛውም ችግር መፍትሄ ልንሰጥዎ እዚህ አለን፤
የደዋይ መለያ ይሁን፣ የስፓም እና የማጭበርበሪያ ጥሪዎችን መከላከል፣ ወይም ለእርስዎ ምቾት የተሠሩ ሌሎች በርካታ ባህሪያት።
በማንኛውም ጊዜ ሊያወሯቸው የማይፈልጓቸውን ሰዎች የስልክ ቁጥሮች በቀላሉ እንዲያግዱ
ሁለት አዳዲስ የደዋይ ማገጃ አማራጮችን አክለናል።
Me እስካሁን የለዎትም? አሁኑኑ ያውርዱ

ቁጥርን ወይም የMe ተጠቃሚን እንዴት ማገድ ወይም እገዳ ማንሳት ይቻላል?
አንድን እውቂያ ወይም የማያውቁትን ቁጥር እንኳ ለማገድ፦ የMe መተግበሪያን ይክፈቱ
የእውቂያውን መገለጫ/የማያውቁትን ቁጥር ይንኩ → የMe መገለጫው ይከፈታል፤
ወደ ታች ወርደው «Block Number» (ቁጥር አግድ) የሚለውን ይንኩ።
ከዚያም ሁለት የማገጃ አማራጮች ያሉት መስኮት ይከፈታል፦
- ቁጥሩን ማገድ፦ ቁጥሩ የጽሑፍ መልእክት ሊልክልዎም ሆነ ሊደውልልዎ አይችልም።
- የMe መገለጫውን ማገድ፦ ተጠቃሚው መገለጫዎን ማየት አይችልም፤ እርስዎም የእሱን አያዩም።
ለአንድ ሰው በሕይወትዎ ውስጥ ሌላ ዕድል ለመስጠት ወስነው እገዳውን ማንሳት ይፈልጋሉ?
የMe አርማን ይንኩ-> «Settings» (ቅንብሮች)->«Blocking Settings» (የማገጃ ቅንብሮች) የሚለውን ይንኩ-> ቁጥሩን ይምረጡ
«Unblock Number» (እገዳ አንሳ) የሚለውን ይንኩ፤ ወይም ወደ ግራ በማንሸራተት እገዳውን ያስተካክሉ።
ጥሪው ካበቃ በኋላ ቁጥርን ወይም የMe ተጠቃሚን ማገድ፤ ከየጥሪ ማጠቃለያ ገጽ (ለAndroid ብቻ)
እንደረዳንዎ ተስፋ እናደርጋለን።
